From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
መስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ (Mesfin & Teddy)
|
|
ልዩ ፡ እትም (Esp)
|
ሰላም ፡ ነው (Selam New)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፫ (2010)
|
ቁጥር (Track):
|
፫ (3)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:35
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የመስፍን ፡ ጉቱ ፡ እና ፡ ቴዎድሮስ ፡ ታደሰ ፡ አልበሞች (Albums by Mesfin & Teddy)
|
|
አዝ፦ ገና ፡ ከጅምሩ ፡ ውድቀቴን ፡ ሲጠባበቁ
በትንሽ ፡ በትልቁ ፡ ድካሜ ፡ ሲሳለቁ (፪x)
ልቤ ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ አበረታሁና
ዛሬ ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ ወጣሁ ፡ ለምሥጋና (፪x)
ጅማሬዬ ፡ ታናሽ ፡ ቢመስል ፡ ፍፃሜዬ ፡ የአማረ ፡ ነው
ያለኝን ፡ ጌታ ፡ ሰምቼ ፡ በቤቱ ፡ ፀንቻለሁ
ሟርተኞች ፡ የሟረቱ ፡ ስንቶች ፡ ተነስተው ፡ ቢሞቱ
የጠራኝ ፡ የቀባኝ ፡ ጌታ ፡ አይጥለኝ ፡ ለአፍታ
ከሳሼ ፡ ያልገባው ፡ አንድ ፡ ነገር
አባቴ ፡ መሆኑን ፡ እግዚአብሔር
ሊከሰኝ ፡ ቢፈልግ ፡ ፍርድ ፡ የእኔ ፡ ነው
ይህን ፡ እንኳን ፡ የማያቅ ፡ ምኑ ፡ ሞኝ ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ ገና ፡ ከጅምሩ ፡ ውድቀቴን ፡ ሲጠባበቁ
በትንሽ ፡ በትልቁ ፡ ድካሜ ፡ ሲሳለቁ (፪x)
ልቤ ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ አበረታሁና
ዛሬ ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ ወጣሁ ፡ ለምሥጋና (፪x)
የማያልፍ ፡ የመሰለኝ ፡ ያ ፡ ዘመን ፡ ካለፈልኝ
ነገንም ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጥዬ ፡ ልዘምር ፡ ተደላድዬ
አቤኔዘር ፡ ሆኖኛልና ፡ ልጨምር ፡ ብዙ ፡ ምሥጋና
ለረዳኝ ፡ ላገዘኝ ፡ ጌታ ፡ ለሆነኝ ፡ እድል ፡ ፈንታ
ከሳሼ ፡ ያልገባው ፡ አንድ ፡ ነገር
አባቴ ፡ መሆኑን ፡ እግዚአብሔር
ሊከሰኝ ፡ ቢፈልግ ፡ ፍርድ ፡ የእኔ ፡ ነው
ይህን ፡ እንኳን ፡ የማያቅ ፡ ምኑ ፡ ሞኝ ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ ገና ፡ ከጅምሩ ፡ ውድቀቴን ፡ ሲጠባበቁ
በትንሽ ፡ በትልቁ ፡ ድካሜ ፡ ሲሳለቁ (፪x)
ልቤ ፡ በጌታ ፡ ላይ ፡ አበረታሁና
ዛሬ ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ ወጣሁ ፡ ለምሥጋና (፪x)
ከሳሼ ፡ ያልገባው ፡ አንድ ፡ ነገር
አባቴ ፡ መሆኑን ፡ እግዚአብሔር
ሊከሰኝ ፡ ቢፈልግ ፡ ፍርድ ፡ የእኔ ፡ ነው
ይህን ፡ እንኳን ፡ የማያቅ ፡ ምኑ ፡ ሞኝ ፡ ነው (፬x)
|